በአዲስ አበባ በሚሊኒየም አደራሽ የእንስሳት ልማትና እና ተዋጽዖ ላይ ያተኮረ አለም አቀፍ አውደ ርዕይ ተከፍቷል። ከምስራቅ አፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ሀገራት የሚገቡ 5፣000 በላይ ጎብኚዎች ይሳተፋሉ። አውደ ርዕይ ለሶስት ቀናት ይቀጥላል።
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) – ከ5፣000 በላይ የምስራቅ አፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ሀገራት ጎብኚዎች የሚሳተፉበት የእንስሳት ልማትና እና የእንስሳት ተዋጽዖ ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አደራሽ ተከፍቷል።
ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው አውደ ርዕይና ጉባኤ ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ተዋናዮች፣ የሀገራት አምባሳደሮች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ይሳተፉበታል። አውደ ርዕይ ሁሉን አቀፍ የእንስሳት እርባታ ቴክኖሎጂ፣ ግብዓትና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል።
የእንስሳት ሀብት የገበያ ሰንሰለቶችን እና የኢንቨስትመንት እድሎች ለማስተዋወቅ የሚያግዝ ነው ተብሏል። በተጨማሪም በዘርፉ ውጤታማ ከሆኑ ሀገራት ልምድ ለመለዋወጥ ና ተሞክሯቸውን ለመቅስም ይሞክራል።
መንግስት በሰጠው ትኩረት ና በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የአራት ዓመት ፕሮግራም የወተት፣ የእንቁላል፣ የዶሮ ስጋ እና የማር ምርቶችን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ግብ አስቀምጦ እየተንቀሳቀሰ ነው።