በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ ያሳለፉ ከ36 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጥተው ወደ ሕጋዊ መስመር ተመልሰዋል ተብሎ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል። ይህ ሥራ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ለመሥራት ያለመ ነው። ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የሚከናወኑ ሪፎርሞች ሀገራዊ አቅም የሚጠናከሩ መሆናቸውን አመልክተዋል።
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) – በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ ያሳለፉ ከ36 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጥተው ወደ ሕጋዊ መስመር ተመልሰዋል ተብሎ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ እየተሰራ ነው። በዘርፉ በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ሀገራዊ አቅም መጠናከሩን አመልክተዋል።
ለአብነትም በአዲስ አበባ በተካሄዱ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ጉባዔዎች የተሳተፉ የውጭ ሀገራት ዜጎች ያለምንም እንከን መስተናገዳቸውን ጠቅሰዋል። በቪዛ አገልግሎት ወደ 188 ሀገራት የመዳረሻ (ኦን አራይቫል ቪዛ) ተጠቃሚዎች ሆነዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተር ይህም የ24 ሰዓት የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት ያለው መሆኑን አመልክተዋል።
ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የተለያዩ የማሻሻያ ርምጃዎች መወሰዳቸውን እና በዚህም በሕገ ወጥ ሰንሰለት የተሰማሩ 26 ሰዎች ተጠያቂ መደረጋቸውን ተናግረዋል። በተያዘው በጀት ዓመት 4 ሚሊየን ፓስፖርት ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉንም ጠቅሰዋል።